Log in

I forgot my password

Who is online?
In total there is 0 user online :: 0 Registered, 0 Hidden and 0 Guests :: 1 Bot

None

[ View the whole list ]


Most users ever online was 11 on Thu Jul 22, 2010 10:46 am
New Sites
አዲስ ሳይት

ኢትዮ ሲንግልስ
Meet Ethiopians Singles | Register Now

ኢትዮ ፎረም
Ethiopians Forum
Latest topics
» ማር ለጤና
Fri Dec 25, 2009 6:39 pm by girreda

» Did you know this? ይህን ያውቁ ኖርዋል ?
Sun Dec 20, 2009 2:51 pm by girreda

» ኢትዮጵያ(ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ)
Sat Dec 19, 2009 3:35 pm by girreda

» ፈገግ ...ፈገግ ....ፈገግታ ...ላንድ ..አፍታ !!!
Sat Dec 19, 2009 10:26 am by girreda

» Men, Love & Sex....
Sun Oct 11, 2009 2:32 pm by Dj Bini

» የእግር ኳስ አጀማመር
Sat Oct 10, 2009 2:38 pm by getahun

» የሰንደቅ ዓላማው ቀን!
Thu Oct 08, 2009 5:47 am by yaredlove

» ለማይክል ጃክሰን ሌላ የቀብር ሥነ ሥርዓት
Tue Oct 06, 2009 6:20 am by yaredlove

» ቢዮንሴና ጋጋ ለኤም ቲቪ ቁንጮነት ይፎካከራሉ
Tue Oct 06, 2009 6:17 am by yaredlove

» ማይክል ጃክሰን ለሞት የሚያደርስ መጠን ያለው መድሃኒት ወስዶ ነበር
Tue Oct 06, 2009 6:09 am by yaredlove

» የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ምንጭ ከየት ነው?
Tue Oct 06, 2009 6:03 am by yaredlove

» ለታላቁ ሽልማት የበቃው የሚሌኒየሙ ሥነ ጥበብ
Tue Oct 06, 2009 5:48 am by yaredlove

» "ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . "
Tue Oct 06, 2009 5:24 am by yaredlove

» Photoshop Tutorials In Amharic
Mon Oct 05, 2009 6:56 am by yaredlove

» በደመና ውስጥ ባክቴሪያ ተገኘ
Sun Oct 04, 2009 12:09 pm by yaredlove

» ከ67 አመታት በኋላ የተገኘው የአልማዝ ቀለበት
Sun Oct 04, 2009 6:26 am by yaredlove

» ንቦች(በታታሪነት ንቦችም ከጉንዳን የሚተናነሱ አይደሉም)
Sun Oct 04, 2009 6:20 am by yaredlove

» ስለ ገንዘብ ከተነገሩ ምሳሌያዊ አነጋገሮች
Sun Oct 04, 2009 6:16 am by yaredlove

» ታዳጊው መስማት ከተሳነው ከ9 ዓመታት በኋላ መስማት ቻለ
Sun Oct 04, 2009 6:11 am by yaredlove

» የስብሀት ወጎች
Sun Oct 04, 2009 6:07 am by yaredlove


የሰንደቅ ዓላማው ቀን!

View previous topic View next topic Go down

የሰንደቅ ዓላማው ቀን!

Post by yaredlove on Thu Oct 08, 2009 5:47 am

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢትዮጵያ ትውፊት መሠረት በክረምቱ መውጫ በመስከረም 25 ቀን 2002 ዓ.ም. በመላ አገሪቱ ለሁለተኛ ጊዜ ተከብሯል፡፡


ሐቻምና በፓርላማው የሥራ ጊዜ ማብቂያ ወር የተከበረው የሰንደቅ ዓላማ ቀን፣ ዘንድሮ ከመክፈቻው ጋር ተያይዞ ተከብሯል፡፡ በዓሉ ቋሚ ቀን ባይኖረውም የበዓሉ ድንበር ግን በአዋጁ ተቀምጧል፡፡

በየኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዲሪ) የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001፣ ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የሚከበረው በየዓመቱ መስከረም ሁለተኛ ሳምንት ሰኞ ይከበራል፤ ይላል፡፡ ይህን አዋጅ ከተከተልን በዓሉ መከበር የነበረበት መስከረም 11 ቀን ሰኞ ነበር፡፡ የሁለተኛ ሳምንት ሰኞ እርሱ ነውና፡፡ በነሐሴ መገባደጃና በጳጉሜንም ሆነ በመስከረም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስለ በዓሉ ሲያስተዋውቅ "የሰንደቅ ዓላማ ቀን በመስከረም ሁለተኛ ሳምንት ሰኞ ይከበራል፡፡ በዚህ መሠረት በዓሉ መስከረም 25 ቀን 2002 ዓ.ም. በአገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል" ብሏል፡፡

መስከረም 25 ቀን ግን 2ኛ ሳምንት ሳይሆን 4ኛውና የመጨረሻው ሳምንት ነው፡፡ ባለፈው ሰኞ የተከበረው በዓሉ ከፓርላማው የሥራ ጊዜ መጀመሪያ ጋር የተገጣጠመ ነው፡፡ በየዓመቱም ሁለቱ ክስተቶች የሚገጥሙ ከሆነ የሰንደቅ ዓላማው አዋጅ የወጣበት ነጋሪት ጋዜጣ አንቀጽ 4 ከኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አዋጅ ቁጥር 1/1987 አንቀጽ 58 ቁጥር 2 ጋር መዋደድ፣ መስማማት ይኖርበታል፡፡ ምክር ቤቱ የሚከፈትበት ጊዜ የመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ላይ መሆኑን ያመለክታልና፡፡

በዓሉ ሲከበር አከባበሩ ሕጉን ጠብቆ የተከተለ ላለመሆኑ አንዳንድ የታዘብናቸው ነጥቦች አሉ፡፡

አንደኛው በተሽከርካሪዎች ላይ ስለሚኖር የሰንደቅ ዓላማ አጠቃቀም ሥነ ሥርዓት ነው፡፡ በአዋጁ መሠረት በየተሽከርካሪው ላይ የሪፐብሊኩን ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል መጠቀም የሚችሉት ርእሰ ብሔሩ፣ ርእሰ መንግሥቱና አዋጁ የፈቀደላቸው ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ናቸው፡፡ በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ከተሞች የታየው ግን በየታክሲው፣ በየባጃጁ፣ በየአውቶቡሱና በሌሎች ተሽከርካሪዎች ሲውለበለብ ታይቷል፡፡

ሌላው ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 13 "የሰንደቅ ልሳን" በሚል ንኡስ ርእስ ሥር "የማንኛውም ሰንደቅ ልሳን (ጫፍ) ግማሽ የክብ አምሳል ይኖረዋል" ተብሎ የተጠቀሰው አልተስተዋለም፡፡ ከጦር ምልክት በቀር፡፡

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ጥንታዊ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይ በ17ኛው ምእት ዓመት የማዕከላዊው መንግሥት መዲና ጎንደር በነበረበት ወቅት የነገሡት አፄ አእላፍ ሰገድ ዮሐንስ ዜና መዋዕል ላይ እንደተፃፈው፣ ንጉሡ ጎጃም ውስጥ ከምትገኘው ደብረ ወርቅ ማርያም ለመታሰቢያ የሰጡዋቸው ሁለት ሰንደቅ ዓላማዎች ቅርፃቸው፣ ይዞታቸው፣ የቀለማቸው ልዩነትና አቀማመጥ ዛሬ ያለውን ዓይነት ነበር፡፡

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን፣ ሰንደቅ ዓላማ ሲወጣና ሲወርድ የሚዘመር መዝሙር ነበር፡፡ ከዘመነ ደርግ ወዲህ ግን ቀርቷል፡፡ ትንሣኤ ይኖረው ይሆን?

በአዲስ አበባ ያኔ የጦር ክፍሎች ባሉበት ባንዲራ ሲወጣና ሲወርድ ጡሩምባ ይሰማ ነበር፡፡ ሲወጣም ሆነ ሲወርድ አንድም ሰው አይነቃነቅም ነበር፤ ከተማው ቀጥ ብሎ ነበር የሚቆመው፡፡ አሁንስ?

yaredlove
Admin

Posts: 52
Join date: 2009-07-12
Age: 18
Location: Ethiopia/Nazareth

View user profile http://www.yared.tk

Back to top Go down

View previous topic View next topic Back to top


Permissions in this forum:
You cannot reply to topics in this forum