Log in

I forgot my password

Who is online?
In total there are 5 users online :: 0 Registered, 0 Hidden and 5 Guests

None

[ View the whole list ]


Most users ever online was 64 on Tue May 06, 2014 11:26 am
New Sites
አዲስ ሳይት

ኢትዮ ሲንግልስ
Meet Ethiopians Singles | Register Now

ኢትዮ ፎረም
Ethiopians Forum
Latest topics
» Sh\\a Sex{wl
Thu Oct 23, 2014 5:13 pm by nenash

» Sh\\a Sex{wl
Thu Oct 23, 2014 5:13 pm by nenash

» Sh\\a Sex{wl
Thu Oct 23, 2014 5:12 pm by nenash

» Sxs Film Hindi
Tue Oct 21, 2014 9:31 pm by nenash

» Kingdom Age Hack Tool V2.5
Tue Oct 21, 2014 8:00 am by nenash

» Ore Wa Kanojo O Shinjiteru! 02 | Checked
Mon Oct 20, 2014 3:57 pm by nenash

» English Conversation With Tamil Meaning Pdf-adds
Sun Oct 19, 2014 2:20 pm by nenash

» English Conversation With Tamil Meaning Pdf-adds
Sun Oct 19, 2014 2:17 pm by nenash

» Hide My Ip Activation Key 5.4
Sun Oct 19, 2014 11:14 am by nenash

» Windows 8 All Editions Activator.exe
Sat Oct 18, 2014 10:01 pm by nenash

» ?????? Anime Anime03 ?? ?? ?? ???? ?? Blu-ray?
Sat Oct 18, 2014 8:08 pm by nenash

» Rhcsa Rhce Red Hat Linux Certification Practice Exams With V
Sat Oct 18, 2014 6:09 pm by nenash

» (2011) Emyumiem Emkazamagreat Download Fevrier French Girl 9
Sat Oct 18, 2014 12:09 pm by nenash

» (2011) Emyumiem Emkazamagreat Download Fevrier French Girl 9
Sat Oct 18, 2014 12:05 pm by nenash

» Download Jason Mraz I'm Yours Free
Thu Oct 16, 2014 1:20 am by nenash

» Download Jason Mraz I'm Yours Free
Thu Oct 16, 2014 1:16 am by nenash

» Aim Bot Bf 3 Download
Wed Oct 15, 2014 9:31 pm by nenash

» Aim Bot Bf 3 Download
Wed Oct 15, 2014 9:24 pm by nenash

» Aim Bot Bf 3 Download
Wed Oct 15, 2014 9:23 pm by nenash

» [Most_popular]_tudung_bj_abg_opis_3gp-adds
Wed Oct 15, 2014 1:06 pm by nenash


ቴዲ አፍሮ በልመና ላይ የተሰማሩ ወገኖችን...

Go down

ቴዲ አፍሮ በልመና ላይ የተሰማሩ ወገኖችን...

Post by yaredlove on Sun Oct 04, 2009 12:02 amቴዲ አፍሮ በልመና ላይ የተሰማሩ ወገኖችን ለመርዳት የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያቀርብ ነው
- ሙሉ ባንዱ ከቺካጎና ሲያትል ይመጣሉ

Wednesday, 30 September 2009

በጎዳና ላይ ለሚተዳደሩና ከተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመምጣት በልመና ላይ የተሰማሩ ወገኖችን ለመርዳት የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ኮንሰርት ጥቅምት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚያቀርብ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) መስከረም 18 ቀን 2002 ዓ.ም. በኢንተር ኮንቲኔታል ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ፡፡


ባለፉት ዓመታት በአበበች ጎበና የሕፃናት ማሳደጊያ ማዕከል ተገኝቶ ወደፊት እርዳታ እንደሚያደርግ ቃል ገብቶ የነበረ ቢሆንም፣ ሳያስበው በተፈጠረ የመታሰር አደጋ በወቅቱ ያሰበውን ማድረግ እንዳልቻለ የገለፀው አርቲስቱ፣ የእስር ጊዜውን ጨርሶ ሲለቀቅ (ከ48 ቀናት በፊት ነሐሴ 7 ቀን 2001 ዓ.ም". ቃሉን ለመፈፀም መንቀሳቀስ መጀመሩን ተናግሯል፡፡

እንደ አርቲስት ቴዎድሮስ (ቴዲ አፍሮ) ገለፃ ኮንሰርት በማዘጋጀት ቃል ገብቶላቸው የነበሩትን ህፃናት ለመርዳት ማሰቡን ከጓደኞቹና የሙያ አጋሮቹ ጋር ሲመካከር፣ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ በጉዳና ላይ የሚኖሩና በልመና ላይ የተሰማሩ ወገኖችን ማስቀደም እንዳለበት እንደተነገረውና በዚህ ዙሪያ ፕሮጀክት ነድፎ የሚንቀሳቀስ ኤልሻዳይ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን የሚባል ድርጅት መኖሩን በማወቁ ኮንሰርቱን ለማዘጋጀት መስማማቱን አስታውቋል፡፡

ቀደም ብሎ ቃል ገብቶላቸው የነበረውን አበበች ጎበና የሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅትን በተመለከተ ለተነሳለት ጥያቄ "እነሱን ከራሴ እረዳለሁ" በማለት የገባውን ቃል እንደሚፈጽምና ወደፊትም የተለያዩ ኮንሰርቶችን በነጻ በማዘጋጀት ችግረኛ ወገኖቹን ለመርዳት ማሰቡን ቴዲ አፍሮ ተናግሯል፡፡

የሙዚቃ ኮንሰርቱ ከውጭ አገር በሚመጡ የራሱ ሙዚቀኞች እንደሚኖሩትና ሙሉ ባንዱ ከችካጎና ሲያትል እንደሚመጡ አርቲስቱ ተናግሯል፡፡

ወጭውን በተመለከተ ለተነሳለት ጥያቄ፣ አርቲስት ቴዎድሮስ በሰጠው ምላሽ፤ አዲካ እና ጂ.ኤም የሚባሉ የአገር ውስጥ ድርጅቶች ስፖንሰር በማፈላለግ ሙሉ ወጪውን እንዲችሉ ኃላፊነቱን መውሰዳቸውን ተናግሮ፣ ለዚህ ለተቀደሰ ሃሳብ ኢትዮጵያውያን ሁሉ (የሚቻላቸው) ስፖንሰር በማድረግ እንዲተባበሩት ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

አዲካ እና ጂ.ኤም በሚያገኙት ስፖንሰር ሙሉ ወጪውን መሸፈን ካልቻሉ፣ እሱ የሙዚቀኞቹን የትራንስፖርትና አጠቃላይ የቆይታ ጊዜ ወጪአቸውን እንደሚችል የገለፀው አርቲስቱ፣ ሁለቱ ድርጅቶች የሙዚቃ መሣሪያና የተለያዩ ወጪዎችን ሊችሉ መስማማታቸውን ተናግሯል፡፡

ከኮንሰርቱ ምን ያህል ገቢ ለመሰብሰብ እንዳቀደ ተጠይቆ፣ "ገቢው ምን ያህል እንደሆነ የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ዝቅተኛ የመግቢያ ክፍያ አሥር ብር መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ከፍተኛው ግን ገና አልታወቀም፡፡ ትልቁ ነገር መልካም ነገር አስበን ማድረጋችንና የሙያ ግዴታችንን መወጣት ነው" በማለት ከገንዘብ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለውና ኤልሻዳይ ዴቨሎፕመንት ማኅበር ብቻ እንደሚመለከተው አብራርቷል፡፡

ኤልሻዳይ ስለሚባለውና በልመና ላይ ስለሚሰራው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ምን ያህል ጥናት እንዳደረገና እንደሚያውቅ ተጠይቆ፤ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለና መናገርም ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለጽ፤ "እኔ የማውቀው የተቸገሩ፣ በልመና ሥራ የሚተዳደሩ ወገኖችን ትንሽም ብትሆን ለማቋቋሚያ የምትረዳ ገቢ ለማሰባሰብና ለመርዳት ነው" በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡

አርቲስቱ ይህ ኮንሰርት ከብዙ አድናቂዎቹ ጋር የሚያገናኘው የአጋጣሚ መድረክ መሆኑንም በመግለጽ፣ ሌላ ጊዜም ከአድናቂዎቹ ጋር የሚያገኘውን ነፃ መድረክ ለማዘጋጀት ሙሉ ፈቃደኛ መሆኑንም ተናግሯል፡፡

ኮንሰርቱ በሚቀርብበት ዕለት በመጀመሪያዎቹ የተወሰኑ ደቂቃዎች፣ ታዋቂውንና ሕይወቱ በድንገት ያለፈውን አርቲስት ጥላሁንን የሚዘክሩ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ አርቲስት ቴዎድሮስ ተናግሯል፡፡

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን በጥቅምት ወር 1999 ዓ.ም. ይበልጣል ደጉ የተባለ ግለሰብ ገጭቶ በመግደል፣ የተገጨንና አደጋ የደረሰበትን ሰው ሳይረዳ በመቅረትና ያለ መንጃ ፈቃድ ሲያስከረክር ተገኝቷል በሚል በተመሰረተበት ክስ እስከ ፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ ተከራክሮ ሁለት ዓመት እስራትና 18ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበት የእስር ጊውን ፈጽሞ ነሐሴ 7 ቀን 2001 ዓ.ም. መፈታቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
avatar
yaredlove
Admin

Posts : 52
Join date : 2009-07-12
Age : 24
Location : Ethiopia/Nazareth

View user profile http://www.yared.tk

Back to top Go down

Back to top


 
Permissions in this forum:
You cannot reply to topics in this forum