Log in
Who is online?
In total there is 0 user online :: 0 Registered, 0 Hidden and 0 Guests :: 1 BotNone
Most users ever online was 11 on Thu Jul 22, 2010 10:46 am
Latest topics
የስብሀት ወጎች
Page 1 of 1 • Share •
የስብሀት ወጎች
ጠይና ይስጥልኝ :: ይህቺ ቤት የጋሽ ስብሀት ገ /እግዚአብሄር የዝክር ቤት ናት :: ሌሎች ስለ ጋሽ ስብሀት ያሉትንና እሱም ከጻፋቸው ውስጥ እጄ የገባውን አለፍ አለፍ እያልኩ አካፍላችኌለሁ ቤት ያፈራውን አብረን እንቀማመስ በማለት ነው :: እናንተም አዋጡ :: ለዛሬ ዘነበ ወላ ካዘጋጀለት የህይወቱ አልበም ውስጥ በመጀመሪያው ገጽ ላይ ያለችዋንና በራሱ የእጅ ጽሁፍ ካሰፈራት አስተያየት ልጀምር ::
በልጅነቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ፎቶ ተነስቼ ሲያሳዩኝ "" ይሄን ነው የምመስለው ?"" ብዬ ገረመኝ :: ፎቶውን ግን አምኘዋለሁ :: ሌሎችን አንስቶ አይቸዋለሁዋ ! ለካ ከውጭ ሲያዩኝ ይሄን ነው የምመስለው :: ሌላ ቀን ደሞ ድምጼን በቴፕ ሰማሁና አሁንም ገረመኝ :: ስናገር እኔ የምሰማው ሌላ የቴፑ ድምጽ ሌላ ! ዘመናት አለፉ (ቀን መቁጠሪያው ግን አመታት አለፉ ይላል ) እኔም ሆንኩ ዘነበ ይህን የምታነቡትን መጽሀፍ ገና በሀሳባችን ሳይመጣ እሱ ስለ ህይወትና ስነ -ጽሁፍ እንዳወራለት ሁኔታዎችን አመቻቸ :: ስናወራ ....ስናወራ ...ስናወራ ...ሳናስበው ይሄ መጽሀፍ ብቅ ማለት ጀመረ :: እኔ ተናገርኩ እሱ መዘገበ ጻፈ :: በስድሳ አመት እድሜዬ ይህ ዘነበ በሚከተሉት ምእራፎች እንደምታነቡት በቃላት ፎቶ አንስቶኝ አየሁ :: ለካ በደግ አይን ሲያዩኝ ይህን እመስላለሁ :: ገርሞኝም አላባራ !!

yaredlove- Admin
- Posts: 52
Join date: 2009-07-12
Age: 18
Location: Ethiopia/Nazareth

እነሆ ቀዳሚና ተከታይ
እነሆ ቀዳሚና ተከታይ የሀላፊውና የመጪው ትውልድ አባል ሆነን ተገናኘን :: ጋሼ የአዲሱ ትውልድ አባል ከቶውንም እማይባልለት መዕራፍ ላይ ደርሷል :: የአላፊው ትውልድ አባል ለመሆን በመጨረሻዋ የህይወት ጠርዝ ላይ ይገኛል :: የእኔም ትውልድ ይከተለዋል :: ህይወት ዕልፍ አዕላፍን ያሸጋገርችው በቅብብሎሽ ነው :: እንደ ወንዝ በምትሀትዋ በውስጣችን ለዘመናት ፈሳለች :: ወደፊትም እንደዚሁ ሂደቱ ይቀጣላል ::
ከዕለታት አንድ ቀን "" ዘነበ ""
"" አቤት ጋሼ ?""
"" ሞትን እንቅደመው ?""
"" እሺ ግን እንዴት ?""
"" ከማውቀው የማስታውሰውን ሁሉ ልንገርህ !""
"" ማለፊያ ""
"" የሚጣፈውንም የማይጣፈውንም ነው የምነግርህ ""
"" እየያዝኩ ነው ""
"" እንቀጥል ሔንድርክ ቫን ሉን ( Hendrik Van Loon) የሚባል የደች ዘር አሜሪካዊ ደራሲ The Wandering Jew የሚባል ልብ -ወለድ ጽፏል :: ባጭሩ ላጫውትህ :: በእኛ ቌንቌ ስትተረጉመው " ከርታታው ይሁዲ " ልትላት ትችላለህ :: ይሁዲው ሲፈርድበት ሊፈታተነው ከማይችለው ቀና ብሎ ሊያየው ከማይገባ ሰው ጋር ለዘላለሙ ተቀያየመ :: "" ድንጋይ ቢወድቅብህ ይጎዳሀል ብትወድቅበትም ይጎዳሀል " እንዲሉ አልኩት ::
" እ ! ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ጌተ -ሰማኒ ጉብታ ሊሰቅሉት መስቀል አሸክመው እየገረፉ ይወስዱታል :: እየተንገዳገደ እየወደቀ እየተነሳ ያዘግማል :: በአካሉ ውስጥ የቀረችው እንጥፍጣፊ ጉልበት ነች :: በዚህ መሀል በዛ ባልታደለ ይሁዲ ደጅ ያልፋል :: የቤቱ ጥላ አጥልታለች :: ጌታ ኢየሱስ እዛ ጋ ትንሽ እፎይ ለማለት ጔጉቶ እየተንገዳገደና እየተወላገደ ጠጋ ሲል ይሁዲው አየውና "" ምን እዚህ ትሽመደመድብናለህ ፈጠን ብለህ ሂድ ! ቀርፋፋ ! "" አለው :: ኢየሱስም ቀና ብሎ አየውና " እኔስ እየሄድኩ ነው አንተ ግን እስከምመለስ እዚሁ ትቆየኛለህ " አለው :: " ያ ከርታታ ይሁዲ አሁንም ባለማችን ላይ በህይወት አለ :: በልዩ ልዩ ሀገር እይተዘዋወረ ይኖራል :: አይሞትም :: ኢየሱስ ወደ አለማችን ዳግም እስኪመጣ ይጠብቀዋል :: የዛን ጊዜም እድለኛ ከሆነ ነው የሞትን ጽዋ የሚጠጣት :: እስከዚያ ድረስ ግን መንከራተቱን ይቀጥላል :: ባለበት ሀገር :: ለረጅም ጊዜ አብረውት የኖሩት ሰዎች ተገርመው " አንተ አታረጅም አትሞትም እንዴ ?' ሲሉት " በቃ አውቀውኛል ማለት ነው ' ይልና ሀገር ቀይሮ የእርግማን ኑሮውን ይቀጥላል :: አንተ ራስህ የአረብ መልክ ያለው ሰው ካጋጠመህ ተጠራጠር :: ምናልባት ከርታታው ይሁዲ ሊሆን ይችላል :: እኔ እንኴን አንድ ቀን ተረት ሰፈር አይቼዋለሁ " አለና ጋሼ ከልቤ አሳቀኝ ::

Page 1 of 1
Permissions in this forum:
You cannot reply to topics in this forum
» Did you know this? ይህን ያውቁ ኖርዋል ?
» ኢትዮጵያ(ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ)
» ፈገግ ...ፈገግ ....ፈገግታ ...ላንድ ..አፍታ !!!
» Men, Love & Sex....
» የእግር ኳስ አጀማመር
» የሰንደቅ ዓላማው ቀን!
» ለማይክል ጃክሰን ሌላ የቀብር ሥነ ሥርዓት
» ቢዮንሴና ጋጋ ለኤም ቲቪ ቁንጮነት ይፎካከራሉ
» ማይክል ጃክሰን ለሞት የሚያደርስ መጠን ያለው መድሃኒት ወስዶ ነበር
» የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ምንጭ ከየት ነው?
» ለታላቁ ሽልማት የበቃው የሚሌኒየሙ ሥነ ጥበብ
» "ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . "
» Photoshop Tutorials In Amharic
» በደመና ውስጥ ባክቴሪያ ተገኘ
» ከ67 አመታት በኋላ የተገኘው የአልማዝ ቀለበት
» ንቦች(በታታሪነት ንቦችም ከጉንዳን የሚተናነሱ አይደሉም)
» ስለ ገንዘብ ከተነገሩ ምሳሌያዊ አነጋገሮች
» ታዳጊው መስማት ከተሳነው ከ9 ዓመታት በኋላ መስማት ቻለ
» የስብሀት ወጎች